Home-አማርኛ

አስተማማኝ የመስመር ላይ የማስተማሪያ መድረክ

የላይትአፕ የፈጠራ አካሄድ የወላጆችን፣ የተማሪዎችን እና አስጠኝዎችን ህይወት ይለውጣል።የወደፊቱን ትውልድ አብረን እናንጻለን። በዚህ አስደሳች ጉዞ ላይ ይቀላቀሉን!

ከቤት ለቤት የማስጠናት አገልግሎት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ያሳስቡዎታል?

እንግዲያውስ ላይትአፕ መፍትሄውን ይዞልዎት መጥቷል!

የልጅዎ ደህንነት

ለልጅዎት የሚሰጠዉ የማጠናከሪያ ትምህርት አብዛኛዉን ጊዜ የእርስዎ ወይንም የቤተሰብዎ የቅርብ ክትትል በሌለበት ሁኔታ ዉስጥ ሰለሚካሄድ የልጅዎ ደህንነት እንደሚያስጨንቅዎት እንረዳለን። በመሆኑም በላይትአፕመድረክ ላይ፣ የክፍለ-ጊዜው ሁነቶች በሙሉ (የቪዲዮ፣ ኦዲዮ፣ ውይይቶች፣ የስክሪንማጋራት ወዘተ) በተንቀሳቃሽ ምስል ስለሚቀረጹ እርስዎ ወይንም የቤተሰብዎ አባል በፈለጉት ጊዜ ገብተው የተቀረጹትን ምስሎች መመልከት ይችላሉ፣ ይህም የልጅዎን ደህንነት ለማረጋገጥ ያስችልዎታል።

የቤተሰብዎ ግላዊ ህይወት እና ደህንነት

ላይትአፕ ከተደጋጋሚ የአስጠኚ ለውጦች የተነሳ የቤተሰብ ግላዊ ህይወት እና ደህንነት ስጋት ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ይገነዘባል።ይህ ስጋትዎ ድርጅታችን ላይትአፕ ይዞልዎት በመጣው ዘመናዊ የልጆች የጥናት ዘዴ ይወገዳል። አገልግሎታችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ታግዞ በርቀት የሚሰጥ ስለሆነ የአስጠኚዎች በአካል መገኘትን ይስቀራል፤ የቤተሰብዎ ግላዊ ህይወት እና ደህንነትም የተጠበቀ ይሆናል።

የትምህርት ቤት ፖሊሲን ማክበር

አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ከልጅዎ ትምህርት ቤት አስጠኚዎችን መቅጠር የሚከለክሉ ምክንያታዊ የሆኑ ፖሊሲዎች ሊኖራቸው እንደሚችል እንገነዘባለን። የላይትአፕ መድረክ በሌሎች የትምህርት ተቋማት ዉስጥ የሚሰሩ አስጠኚዎችን የመቅጠር እድልን ይሰጣል።እነዚህ አስጠኚዎች በስልክዎ፣ በታብሌትዎ ወይም በላፕቶፕዎ በኩል በቀላሉ ተደራሽ ናቸው፣ ይህም ከቤትዎ ምቾት ሆነው ከእነሱ ጋር እንዲገናኙ ያስችልዎታል።

ልዩ ለወላጆች የሚሰጥ የክህሎት እገዛ

ላይትአፕ የልጅዎን ትምህርት ለመከታተልና ለመደገፍ የሚያስፈልግዎትን መሰረታዊ እውቀትና ክህሎት ለማጎልበት የሚረዱ ልዩ ስልጠናዎችን በራሱ ወጪ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎቸ ይሰጥዎታል።

የ24 ሰዓታት የማያቋርጥ አገልግሎት

የቤት ለቤት ጥናት አገልግሎት ከመደበኛው የትምህርት ጊዜ በኋላ ለጥቂት ሰዓታት ተሰጥቶ የሚቋረጥ፣ በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ደግሞ ለተወሰኑ ሰዓታት ብቻ የሚካሄድ ነው፤ የእኛ መድረክ ግን በቀን 24 ሰዓት፥ በሳምንት ሰባቱንም ቀናት፥ በዓመት 365 ቀናትና ሌሊት መስመር ላይ ይገኛል። ከእርስዎ የሚጠበቀው ለልጅዎት ተስማሚ የሆነዉን ጊዜ መወሰንና በዚህ ሰዓት ዉስጥ አስጠኚዎቸን መምረጥ ብቻ ነው።

የአስጠኚዎቸ በበቂ ሁኔታ መገኘት

ላይትአፕ ለልጅዎ ተስማሚ የሆነ አስጠኚ ሲፈልጉ የሚያጋጥምዎትን ተግዳሮቶችይረዳል። የላይትአፕ መድረክ እርስዎን ታዋቂ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ የላቀ ብቃት ካላቸው አስጠኚዎች ጋር ያገናኝዎታል፣ ይህም በልጅዎ ትምህርት ቤት ውስጥ ያለውን የአስጠኚዎች ክፍተት ወይም በሌላ ቦታ ያሉትን ውስን አማራጮች ከመሙላት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የዋጋ ተመጣጣኝነት

ላይትአፕ ለዘመናት ሲሰራበት ለኖረው ዉድ የቤት ለቤት የማስጠናት አገልግሎት አማራጭ የሆነ ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ዘመናዊ አገልግሎት ይዞልዎት ቀርቧል።በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ከሚገኙ ታዋቂ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን አስጠኚዎች ማግኘት የምትችሉበትን ሁኔታ አመቻችቷል።ስለሆነም የገንዘብ አቅምዎትን የሚመጥን አስጠኚ እዲያገኙ ያስችልዎታል። በተጨማሪም የእኛ ስርዓት አንድ አስጠኚ በአንድ ጊዜ ሁለት ወይም ሶስት ልጆችን የሚያስጠናበት/የምታስጠናበት አማራጭ ስለሚኖረው ለአንድ ሰዓት የሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ቅናሽ ይኖረዋል።

የላይትአፕን መድርክ ለመጠቀም አስፈላጊ ነገሮች

ዲጂታል የመጻፊያ መሳሪያዎች

በተማሪው እና በአስጠኚው መካከል እንከን -የለሽ መስተጋብር ለመፍጠር፣ በቅድሚያ እንደ ብዕረ ታብሌት፣ ብዕረ ላፕቶፕ፣ ወይም ዲጂታል የእስክሪብቶ ታብሌቶችን የመሳሰሉ ዲጂታል የመፃፊያ መሳሪያዎችን ማግኘት በጣም አስፈላጊ ነው። ከእነዚህ መካከል አንዱም ከሌለዎት የእኛ መድረክ -ላይትአፕ ፣ ዲጂታል ብዕረ ታብሌቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ይችላል። ላይትአፕ የሚያቀርብልዎት ብዕረ ታብሌት ስክሪን የሌለው ቢሆንም ከማንኛውም ታብሌት፣ ላፕቶፕ ወይም ዴስክቶፕ ኮምፒውተር ጋር ተስማሚ በመሆኑ፣ ምቹ የጽሑፍ አገልግሎት ይሰጣል።

አስተማማኝ የኢንተርኔት ግንኙነት

ምቹ የመስመር ላይ (ኦንላይን) የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት የማይቆራረጥ አስተማማኝ የበይነመረብ ግንኙነት የግድ ያስፈልጋል። ስለዚህ በገመድ ወይንም ገመድ አልባ የሚገናኝ ቢያንስ 2 ሜጋ ባይት ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት መስመር እንዲኖርዎት ያስፈልጋል። የዋይ ፋይ አገልግሎትን በሚጋራ ቤተሰብ ውስጥ፣ የጥናቱ ክፍለ ጊዜ እስኪጠናቀቅ ድረስ ሌሎች የዋይፋዩ ተጠቀሚዎች ዋይፋዩን መጠቀማቸውን ለጊዜዉ ማቆም ወይም ለሁሉም ቤተሰብ በቂ የሆነ ኢንተርኔት ፍጥነት መግዛት አስፈላጊ ነዉ። ከሞባይል የሚጋራን ኢንተርኔት (ሆትስፖት) መጠቀምም አይመከርም። ነገር ግን ስልኩ ለኢንተርኔት አገልግሎት ብቻ የሚያገለግል ከሆነ (ማለትም የስልክ ጥሪዎችን የማይቀበል ከሆነ) ያለምንም የአገልግሎት መቆራረጥ የጥናት ፕሮግራሙን ማስኬድ ይቻላል።

አሁኑኑ እንዲመዘገቡ እናበረታታዎታለን

ቡዙ ጊዜ ሳያጠፉ፣ የስኬት ጉዞዎን ይጀምሩ። መለያዎን አሁን ይፍጠሩ።